በጀርመን አገር በሙኒክ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደኢትዮጵያዊያን በሀገራቸውየኮሮናቫይረስ ወረርሺኝን ለመከላከል እንዲቻል 8558,00€ የገንዝብ እርዳታ አደረጉ

በጀርመን አገር በሙኒክ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንደ ሌሎች በውጭ አገር የሚኖሩ ወገኖቻቸው በኢትዮጵያ የኮረና ቫይረስ ወረርሺኝን ለመከላከል በሚደረገው ርብርብ ላይ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ከፍራንክፈርት የኢፌዲሪ ኮንሱላት ጽ/ቤት የቀረበውን የዜግነት ጥሪ መነሻ በማድረግ በየኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ በሙኒክ አስተባባሪነት ባለፉት ሳምንታት በኦን ላይን (Online) የተጀመረው የገንዘብ እርዳታ ማሰባሰብ የደረሰበትን ደረጃ በሚመለከት  የእያንዳንዱ ልገሳ ያደረጉ ወገኖችን ስምና የለገሱትን የገንዘብ መጠን የታዳጊ ወጣቶችን አስተዋፅኦ ጭምር በዝርዝር ለህብረተሰቡ ግልጽነት ባለው መንገድ በሰንጠርዥ በማቅረብ አሳውቀዋል ።
የኮሚዩኒቲው ሊ/መንበር ወ/ሮ ዘነብወርቅ አድነው በአፕሪል  (እኤአ በ24.04.2020 )የኮሚዩኒቲው የስራ አመራር ኮሚቴ ከአባላቱ ጋር የሚገናኝበት „የኮሚዩኒቲው አመራር መልዕክት ማስተላለፊያ “ የWhatsApp ግሩፕ ላይ የመጨረሻውን ውጤት ሲገልጹ ባጠቃላይ የተዋጣው ገንዝብ 8558,00€ ( ስምንት ሺህ አምስት መቶ ሃምሳ ስምንት ዩሮ )የኮሚዩኒቲው የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝን ለመከላከል እንዲቻል በፍራንክፈርት የኢፌዲሪ ኮንሱላት ጽ/ቤት በፍራንክፈርትና አካባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ገንዘብ ለማሰባስብ ታቅዶ በተከፈተው የባንክ አካውንት  ያስተላለፈ መሆኑን ገልጸዋል።

(ከታዳጊ ወጣቶች ከቀረቡ የእርዳታ ተሳታፎዎች ለአብነት ያህል የቀረበ )

በዚሁ አጋጣሚውን በመጠቀም እንደ ኮሚዩኒቲ በጋራ እንቁም መርሀችን በእጅጉ ውጤታማ አድርጎናል። መተባበርና በጋራ መቆም ምንግዜም ለውጤት ያበቃል። ያየነውም ይሄንኑ ነው። ሀገራዊ ጥሪ ምንግዜም የወገን ምላሽ ያስፈልገዋልና  ለጠየቅናችሁ ጥያቄ ስለሰጣችሁን አፋጣኝ ምላሽ ምንም  ችግሩ የጋራችን ቢሆንም አኩርታችሁናልና አክብሮታችን  እጅግ የላቀ ነው። በተጨማሪም ታዳጊና ወጣት ልጆቻችን ላደረጉት ልብ የሚነካ ተሳትፎ ሳናመሰግናቸውና ተባረኩልን ለበለጠ ማዕረግ ያደርሳችሁ መልካም የስራችሁን ውጤት ለማየትም ያብቃችሁ ለማለት እንወዳለን ሲሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።