የኢትዮጵያ አዲስ አመት 2012 ዓ/ም በሙኒክ ከተማ በድምቀት ተከብሯል

ethiopian new year 2012

በጀርመን አገር በሙኒክ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በጥቅምት 1 ቀን 2012 ዓ/ም ( እኤአ በኦክቶበር 12.2019) በኮሚኒዩቲያቸው አስተባባሪነት በኢትዮጵያውያን የዘመን አቆጣጠር አዲሱን ዓመት 2012ዓ/ምን  ባንድ ላይ ተስባስበው ቤተስባዊ መልክ ባለውና በደመቀ ሁኔታ አክብረዋል።

በአለቱም የኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ በሙኒክ ከተመሰረተበት ረጂም ዓመታት ጀምሮ በተለያዩ ወቅቶች ማህበሩን በመምራትና በፈቃደኝነት በማስተባበር ንቁ ተሳትፎ ሲያደርጉ የቆዩ የማህበሩ አባላት በበአሉ ላይ በተገኙት ታዳሚዎች ፊት ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።

የበአሉን አከባበር በሚመለክት አጠቃላይ ግንዛቤ ለማግኘት ከዚህ ጽሁፍ ጋር የተቀመጡትን ምስሎች የመልከቱ።