ከመፃህፍት አለም ታላቁ ጥቁር ከተሰኘ መፅሐፍ የተወሰደ

ከዚህ ቀጥሎ በተለያዩ ክፍሎች የሚቀርቡት ጽሁፎች ከዚህ በላይ በምስል ከተቀመጠው ከለመድናቸውና ካነበብናቸው ለየት ያሉ ያልተሰሙ የአድዋ ድልና የአጤ ምኒሊክ ታሪኮችን ይዞ ለህዝብ ከቀረበው የአቶ ንጉሴ አየለ ተካ ‚ታላቁ ጥቁር ‚ የተሰኘ መፅሐፍ የተወሰዱ መሆናቸውን አስቀድመን ለመግለፅ እንወዳለን ።

ልክ በዛሬው ቀን ፌብሩዋሪ 1,1094 እኤአ

የምዕራቡ ዓለም ሪፓርተሮች ምን ዘገቡ?

ሮበርት ስኪነርና አብረውት የነበሩት ባልደረቦቹ ከኢትዮጵያ ድሬዳዋ ፣ በጂቡቲ ከዚያም በቪክቶሪያ በተሰኘች መረከብ  አድርገው. ስኪነር ከ5አመታት በላይ ወደ ሰራባት ማርሴይ (ፈረንሳይ) ሲደርስ

በፓሪስ የአሜሪካን ኤምባሲ ተወካይና  ብዙ ሌሎች ሠዎች „እንኳን ደህና መጣህ“ ለማለት ተሰብስበዋል ።ከስድስት ወራት በላይ የተለያት ባለቤቱ ሄለንም ነበረች።ነገር ግን ስለኢትዮጵያና ስለ ጥቁሩ የአቢሲኒያ ንጉስ ለመስማትና ሪፖርት ለማድረግ የተሰበሰቡት  የአውሮፓና የአሜሪካን የዜና ሪፓርተሮች ቦታውን አጨናንቀውት ነበር።

ስኪነር በሪፓርተሮች ተከበበ!

አይጣል ነው የስራ ሰው መሆን።በምዕራቡ አለም ደንብ ጋዜጠኞችም ይከበራሉና ተልዕኮውን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠት ነበረበት።

በኋላ ዜናውን ካወጡት ሪፖርቶች ለመረዳት እንደተቻለው መግለጫው ለጥያቄና መልስ ዕድል ከመስጠቱም በላይ ፣ስኪነር ስለተልዕኮውና ክንውኖቹ፣እንዲሁም ስለ አፄ ምኒሊክ ይናገር የነበረው በጋለ ስሜት ነበር።

ይህ ከተልዕኮው በሁዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከራሱ ከመልዕክተኛው የተሰጠ መግለጫ

ከፌብርዋሪ 1ቀን (1904) ጀምሮ በአውሮፓና በአሜሪካ ጋዜጦች ታትሞ ወጣ።

ከብዙዎቹ የተጠቀሱት ሪፓርቶች ውስጥ  ለዛሬዋ ቀን ማስታወሻነት አንድ ሁለቱን ብቻ  እንመልከትና ቀሪዎቹን ሰሞኑን እንደ አመቺነቱ እንመለከታለን።

የዋሽንግተን ታይምስ

የስኪነርን መግለጫ ሲያቀርበው „ስኪነር በተልዐኮው ውጤት አሳይቷል።…. ዩናይትድ ስቴትስ በአፍሪካ ብሩህ መፃዒ‐ዕድል እንደሚጠብቃትም አስታወቀ“ በማለት በዝርዝር ያትታል።

„ምኒሊክ አሜሪካውያንን እንደሚቀበሉ ስኪነር  ገለጸ“ ያለው የሴንት ሉዊሱ „“ግሎብ ዲሞክራት““ ነበር። ይህ ሪፓርት ሲቀጥልም „ንጉሱ በአቢሲኒያ ውስጥ ምን አይነት የንግድ ዕድሎች እንዳሉ ለአሜሪካውያን ለማሳየት ያስባሉ“… „በዩኤስ መንግስት ወደ አቢሲኒያ ተልኮ የነበረው ቆንሲል ስኪነር በትናንትናው ዕለት ማርሴይ ገብቷል።እርሱና የቡድኑ አባላት ንጉሠ ነገሥቱ ባደረጉላቸው አቀባበልና መስተንግዶ እጅግ ተደስተዋል።..“ካለ በሁዋላ „አቢሲኒያ በፍጥነት ዘመናዊ ሥልጣኔን እያስገባችትገኛለች። መንገዶች፣ድልድዮች፣ቴሌፎን፣ቴሌግራፍና የውሀ አገልግሎት በዘመናዊ መልክ ለማስፋፋት ስራው መጀመሩን ስመለከት ጠቅሶ በዚህ ጥረታቸው አበሾች „የአፍሪካ ጃፓን““ማለት እንደሚቻል ገልፇል።

ይቀጥላል

በቸር ይግጠመን