ከመፃህፍት አለም ታላቁ ጥቁር ከተሰኘ መፅሐፍ የተወሰደ

ፌብሩዋሪ 1ቀን 2020 በ23: 57 ሰአት ተፃፈ

ውድ ወገኖች እንዴት ከርማችሁዋል?

በአለፈው ፌብሩዋሪ 1ቀን ልክ በዚያችው ዕለት ከ116 አመታት በፊት በኢትዮጵያና በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መካከል የዲፕሎማሲየንግድ ግኑኝነት ለመጀመር እንዲያስችል በመንግሥት ተቀብሎ ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ የስድስት ወራት ቆይታ አድርጎ በመመለስ ለአውሮፓና ለአሜሪካን ሜዲያዎች የሰጠውን መግለጫና የተለያዩ ጋዜጦች ኢትዮጵያና የወቅቱን ነጉስ አፄ ምኒሊክን እንዴት እያዳደነቁ እንደዘገቡት አቶ ንጉሴ አየለ ተካ “ታላቁ ጥቁር”. በሚል ከፃፉት መፅሀፍ ቀንጨብ አድርገን ተመልክተናል።

 ወደ ሌላ ስሜትን የሚስቡና አስገራሚ የምኒሊክና የአገራችን የወቅቱ ታሪክ ከማለፋችን በፊት ስኪነር ለሜዲያዎች መግለጫ ሲሰጥ ምኒሊክን እንዴት ገለፃቸው?

“የኒወርክ ሰን” (Newyork sun)የተሰኘ ጋዜጣ በፈብሩዋረ 4ቀን 1904ዓ.ም.

ሰፊ ጽሁፍ እንዳአቀረበ እንመልከት ።።

 ርዕሱ “KING MINILIK II” የሚል ሲሆን እንደሚከተለው ዘግቦታል።

“…. ምኒሊክ ሁሌም ለውጭ ሠዎች በኦፊሴላዊ ግኑኝነት ላይ ትሁት፣ተግባቢና ግርማ ሞገስ ያላቸው በመሆናቸው የሚወሰድ ስሜት ያሳድራሉ። በአካላቸው የሚማርክ ነገር ኖሯቸው አይደለም።ቁመታቸው መካከለኛ ሆኖ ጥቁር ፊታቸው የሚከብድና በፈንጣጣ የተጠበሰ ነው። ግን ብልህነትና {Intelledence} ብዙውን ጊዜ አግባብ ያለው ቀልደኝነታቸው (Good Humor) አድራሻውን ነገር ይሸፍነዋል።ስለአገራቸው በአደረጉት ነገር በዜጎቻቸውም በውጭ ሰዎችም እንዲከበሩ አድርጓል። አቢሲኒያ መጥፎም ጊዜ ቢኖራት እርግጥ በማዕድኗ፣ለግብርና ባላት አመቺነት. በአፍሪካ አንዷ የተፈጥሮ ሀብታም በመሆኗ ሁሌም የዓለምን ትኩረት የምትስብ አገር ናት።ብልህ፣ጥሩና ችሎታ ያለው መሪ ሲኖር ደግሞ በከፊል ያልሰለጠነ የሚባል የአፍሪካ አገር ሊኖር አይችልም።… ” ይልማ በመወጠል ሲያትት; ‐

“ምኒሊክ ለአገራቸው ያስገኙት ዋና ነገር ሰላም ነው።ቀደም ሲል አገሪቱ በተለያዩ ጎሳና የአካባቢ ገዢዎች ተከፋፍላ ነበር ።ዛሬ አቢሲኒያ አንድ እና ያልተከፋፈለች ነች። ገዢዋም እርሳቸው ናቸው። (Abisinia is to‐day one and undivided, and he is its ruler) ንጉሡ ፈላጭ ቆራጭ (sbsolute) ቢሆኑም በዙሪያቸው ያሰባሰቧቸው አማካሪዎች በተለያየ ጎሣ የወጡና የውጭ አገርተወላጆች ጭምር ናቸው። የሚወስኑትም የሁሉንም ምክር አገላብጠው አይተው ነው።ካፒቴይን ዊልቢ (wellby) ስለእሳቸው ከልቡ ሲናገር “እርሳቸው ካለፉት የአቢሲኒያ ገዢዎች ሁሉ እጅግ የቀደሙ ናቸው።” (He is far in advance of any abisinian ruler) ብሏል”

“ምኒሊክ በጥበብ (Wsdom) ነው ያደጉት።ቀደም ሲል ከነበሩት ሐይሎች ጋር ግጭት ውስጥ መግባት አይልጉም ነበር።ሆኖም ያኔ ሲናገሩ “እግዚአብሔር ዕድሜና አቅም ከሰጠኝ የኢትዮጵያን ጠረፍ እስከ ካርቱምና እስከ ቪክቶሪያ ቢያንስ (Victoria Nyanza) አስፍቼ የጥንቱንና ትክክለኛውን የኢትዮጵያን ወሰን እመልሳለሁ ።ብለው ነበር ። አስተዋይና አመዘዛኝ በሆኑ የህዝብ ፖሊሲዎቻቸው ፣ሁዋላ ታዋቂ ከሆኑት ሰው እነኚህ ቃላት ቀደም ካለው ታሪካቸው መስማት የሚደንቅ ነው።ለዚህ ሃሳባቸው ችኩል እርምጃ ውስጥ ገብተው አያውቁም. ።. “

“የአገሪቱ የውጪ ንግድ ከ80,000$ ወደ ሚሊዮኖች ያደገው በቀጥታ ምኒልክ ባመቻቹት ሁኔታ ነው። እርግጥ የአቢሲኒያ እድገተሸገና ጥሬ ነው። ግን በአገር ውስጥ በሚደረገው እርምጃና ከሌላው ዓለም ጋር የጀመሩት ሠፊ ስራ የንግድ ግኑኙነት ካልተቋረጠ አያያዛቸው ወደ ታላቅ እድገት የሚያመራ ነው።ንጉሡ አቢሲኒያን ከፍ ወዳለ የሥልጣኔ ደረጃ ለማድረስ የሚያደርጉትን ጥረት ሁሉም አገሮች በአዘኔታና በፍላጎት እየተመለከቱት ነው። (….. all nations are watching with sympathy and interest the efforts of tge king to place Abysinia on the higher pkane of civilization. )” በማለት የኒዮርክ ሰን ጋዜጣ በሰፊው መዘገቡን አቶ ንጉሴ ተካ አየለ በ2010 ዓም “ታላቁ ጥቁር” በሚል በፃፉት መፅሀፍ1 በገፅ 274 ና 275 ላይ ዘርዝረው ለንባብ አብቅተዋል።

 ውድ ወገኖች ሜዲያዎቹ የመጀመሪያውን ወደ ኢትዮጵያ በመንግሥት የተላከ በፈረንሳይ ማርሴይ ቆንስላ የነበረው ፒት ስኪነር የሰጠውን መግለጫ አስመልክቶ በብዛት የዘገቡ ሲሆን ይበልጥ ፍላጎት ያላቸው አንባቢያን የአቶ ንጉሴ አየለ መፅሐፍ በገበያ ላይ የሚገኝ ስለሆነ እንዲያነቡእያሳሰብኩ በሜዲያዎቹ ዘገባ ብቻ ጊዜ ላለመውሰድ ወደ ሌሎች ስሜትን የሚስቡ በመፅሀፉ የተገለጹ ታሪኮች እናልፋለን።

*ለመሆኑ ፒት ስኪነር ወደ አቢሲኒያ ፣ወደ ምኒሊክ ሲሄድ ምን ይዞ ሄደ?

*ስኪነር ከስድስት ወር የአቢሲኒያ ቆይታ በሁዋላ ለዘመናዊቷ ዩናይትድስቴትስ {ለፕሬዚዳንት ሩዝቬልት} ከምኒሊክ የተላከ ምን ስጦታ ይዞ ሄደ?

አቶ ንጉሤ አየለ በጠንካራ ማስረጃ ያቀረቡትን አስገራሚ ታሪክ

ይህ በሚቀጥለው የምንመለከተው ይሆናል።

ቸር ይግጠመን