ከመፃህፍት አለም ታላቁ ጥቁር ከተሰኘ መፅሐፍ የተወሰደ

መስፍን ጳውሎስ

የኢትዮጵያና ዩናይትድ ስቴት አሜሪካ መካከል ዲፕሎማሲያዊ ግኑኝነት እንዲጀመር ከፍተኛ ጥረት በማድረግና የወቅቱን የአሜሪካን መሪ ፕሬዘዳንት ሩዝቬልትንና ካቢኔያቸውን አሳምኖ በአድዋ ድል መነሻ ታዋቂ የሆኑትን ዓለም ያደነቃቸው የኢትዮጵያ ንጉስ አፄ ምኒሊክጋ ተልኮ አስገረራሚ ጉብኝት አድርጎ የተመለሰው ሮበርት ፒት ስኪነር የተባለ ሰው የዛሬ 116 አመት ታሪክ በእርግጠም መሳጭ ነው።

ሰለሮበርት ፒት ስኪነር እና አቶ ንጉሴ አየለ የዚህን ሰው ታሪክ ለማግኘት የሄዱበትን  መቃብሩንም ያገኙበት አስገራሚ ሂደት ለሌላ ጊዜ አቆይተን ልክ በዛሬዋ ፌብሪዋሪ አንድ ቀን የዛሬ 116አመት የአሜሪካን ጋዜጦች የዘገቡትን በመመልከት እንጀምር በሚቀጥሉት ጊዜያት (ቀናት) ደግሞ እንደ አመቺነቱ በመፅሀፉ ከተጠቀሱ የአፄ ምኒልክና የሀገራችን ሁኔታ የሚያሳዩ አስገራሚ የሆኑትን ወደፊትም ወደሇላም እያልን ለመቃኘት እንሞክራለን ።

በመጨረሻም በተለያዩ የአለማችን በተለይም በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካን የተለያየ የህትመት ውጤቶች (ጋዜጦች) ተጽፈዋል ተብለው የተጠቀሱት ከዚህ ጽሁፍ በመከተል የሚወጡት ጽሁፎች ሁሉ ደራሲው አቶ ንጉሴ ከቦታ ወደ ቦታ ተንከራተው በተለያዩ የቅርስና የመፃህፍት ቤተ መዛግብት እያስፈለጉ በአይናቸው አይተው፣ በእጃቸው ዳሰው በፎቶግራፍ አስደግፈው ያወጧቸው እርግጠኛ

በማስረጃ የቀረቡ በመሆናቸው ተአማኒነታቸውን ሙሉ ያደርገዋል።

መስፍን ጳውሎስ

መልካም ንባብ።

ይቀጥላል