ከመፃህፍት አለም ታላቁ ጥቁር ከተሰኘ መፅሐፍ የተወሰደ

መስፍን ጳውሎስ

ፌብሩዋሪ 17,2020

ውድ በሙኒክ የኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ አባላት ወገኖቼ ስለ አድዋ ጦረነትና ስለ አፄ ምንሊክ  ለትውልድ መተላለፍ  ያለበትን ያህል ያለ መሰራቱን መረዳት ይቻላል።

ይህንንም ለመረዳት በውጪው አለም የተፃፉትን መፃህፍትና ጋዜጦች እንዲሁም ቅርሳቅርሶች አያፈላለጉ የሚመራመሩ እንደ አቶ ንጉሴ አየለ ያሉ የታሪክ ተመራማሪዎች ያስፈልጋሉ።

ባለፈው በተለያዩ አጫጭር ጽሁፎች ከአቶ ንጉሴ  “ታላቁ ጥቁር” መፅሀፍ እንዳካፈልኳችሁ ሁሉ ዛሬም በአሜሪካን አገር የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎችንና ጋዜጦችን በመጥቀስ በመፅሀፉ ከተጠቀሱት ጥቂቶቹን እንመልከት::— ገፅ 108

“በ890ዎቹ ዓመታት በምዕራቡ ዓለም ትልቅ ትኩረት ያገኘውና ብዙ ወቅታዊ ጽሁፎች የተዥጎደጎዱለት ኢትዮጵያዊ ጉዳይ አድዋ ነበር።

“የ896 የአድዋ ጦርነትና ውጤቱ ብዙ ተፅፎለታል ።ከጦርነቱ በፊት የነበረው ጭቅጭቅ ሳይቀር ተነስቷል።በአጠቃላይ ስለአድዋ ጦርነትና ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ በአሜሪካ የወጡት ጽሁፎች ቢሰራባቸው ራሱን የቻለ ትልቅ መፅሐፍ ይወጣቸዋል።

በኢትዮጵያና በጣሊያን መካከል የታየው የፓለቲካና ወታደራዊ ትግል በጋዜጦች እንደተዘገበው ከሆነ ምኒሊክንና አገራቸውን በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ድርሻ ነበረው።”

እንዲያውም የምኒሊክ ምስል በሰዓሊ ንድፍም ሆነ በፎቶግራፍ መልክ ለምዕረቡ ዓለም ተደጋግሞ በብዛት መቅረብ የጀመረው ያኔ ነው ማለት ይቻላል ።….. በምስል ረገድ ከቀረቡት መሀል በኒውዮርክ ታይምስ አንዱ መሆኑንናታይምስ በአድዋው ጦርነት ዙሪያ በተለያዩ ቀናት ከዘገባቸው ከ50ያላነሱ ዜና‐ሪፖርቶች መሀል በማርች 7 ቀን 1896 ዓም ከወጣው ጽሁፍ ጋር የሚከተለውን የምኒሊክንና የጣይቱን ምስል አስደግፎ ነበር።በማለት አቶ ንጉሴ በመፅሀፋቸው በገጽ 109 ላይ የጋዜጠውን ምስል አቅርበውልናል።

ይቀጥላል

 ፌብሩዋሪ 27/2020

መስፍን ጳውሎስ