የወንድማችን የአቶ ብሩክ ማሞ የመታሰቢያ ሃውልት ምርቃት

በሙኒክ ነዋሪ የነበረው ሀገር ወዳዱ ወንድማችን አቶ ብሩክ ማሞ ወደ ውድ ሀገሩ ወደ ኢትዮጵያ ሄዶ ባደረበት ድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም መለየቱን አስመልክቶ ኮሚዩኒቲያችን አስተባባሪነት በኖቬምበር 14 ቀን 2020 እኤአ የፀሎትና የስንብት ስነስርዓት መደረጉ ይታወሳል ።

በዚህ ስነስርዓት ላይ ከወዳጅ ጓደኞቹ ጥያቄ በመነሳት  ለወንድማችን የአቶ ብሩክ ማሞ የመታሰቢያ ሀውልት ማሰሪያ ይሆን ዘንድ በኮሚዩኒቲያችን በኩል የተሰበሰበውን (2000.00Euro) 100.000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ለቤተሰቦቹ አስተላልፈን አነሆ የሀውልቱ ስራ ተጠናቆ ቤተሰቦቹ በተገኙበት የተመረቀ መሆኑን የምናሳውቃችሁ ላሳያችሁት ወገናዊ ትብብር ከልብ በማመስገን  ነው።

የወንድማችንን ነፍስ ይማር! 

ለቤተሰቦቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን ይስጥልን! 

በሙኒክ የኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ