ግድቡ የኔ ነው!

በመስፍን ጳውሎስ

የህዳሴ ግድቡ ስራ መጠናቀቅ የአንድ ብሄር፣ሀይማኖት ወይም የፖለቲካ አመለካከት ያለው ህብረተሰብ ብቻ ፍላጎት ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያውያን መሆኑ ግልጽ ነው።
ከዚህ የግድብ ስራ ጋር የተያያዙ እንቅስቃሴዎች ላይ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተግባራዊ አስተዋጽኦ ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው በያሉበት ከሚያደርጉት እንቅስቃሴዎች መገንዘብ ይቻላል።
በዚሁ መሰረት በጀርመን አገር የህዳሴውን ግድብ ስራ ድጋፍ በሚመለከት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ማስተባበር የሚያስችል የተለያዩ ህብረተሰባችንን ከሚወክሉ ልዩ ልዩ ማህበራትና ታዋቂ ወገኖች የተካተቱበት ግብረሃይል ተቋቁሞ ስራ የጀመረ ሲሆን ግብረሃይሉ ከነደፋቸው ዘርፈ ብዙ የስራ ዕቅዶቹ አንዱ የህዳሴውን ግድብ አስመልክቶ በተለያዩ የታሪክ፣የጥናትና ሌሎች የስነፅሁፍ ውጤቶችን በመፅሔት መልክ በማሳተም ህብረተሰባችን ስለዓባይ ወንዝና ስለህዳሴ ግድብ ያለውን ግንዛቤ እንዲያሳድግና ከመፅሄቱም ሺያጭ የሚገኘውን ትርፍ ለህዳሴው ግድብ ስራ ማዋል እንዲያስችል ማድረግ በመሆኑ የተለያዩ በጀርመን የሚኖሩ ሀገር ወዳድ ወገኖችን በማስተባበር? * ግድቡ የኔ ነው * የሚል ርዕስ የተሰጠው መፅሔት

ለህትመት እንዲበቃ ተደርጎ በየአካባቢው በሚገኙ የተለያዩ የኢትዮጵያውያን ማህበራት ተሰራጭቶ በመሸጥ ላይ ይገኛል።
ስለዚህም ሀገሩን የሚወድ ዜጋ ሁሉ ትንሿን አስተዋፅኦ እንዲያደርግ አመቺ ሁኔታን የፈጠረ መሆኑን በመግለጽ የሙኒክና አካባቢው የኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ መጽሔቱን በደመቀ መርሀ ግብር አዘጋጅቶ ለማስተዋወቅና ለመሸጥ ዝግጅት እያደረገ መሆኑና እስከዚያው መጽሔቱን ለማከፋፈል ከወከላቸው የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላት መግዛት እንደሚቻል በማህበራዊ ሜዲያ ገልጿል።
ስለዚህም ሀገር ወዳድ የሆንን ወገኖች ሁሉ ይህን „ግድቡ የኔ ነው“ የሚሰኝ መፅሐፀት ለራሳችንና ለሌሎች ወዳጆቻችን ገዝተን በስጦታነት በማበርከት አሻራችንን ለማሳረፍ እንድንችል ተጋብዘናልና ከግብዣው እንቋደስ።


የኢትዮጵያ ህዝብ የህዳሴን ግድብ በመተባበርና በቁርጠኝነት ለፍፃሜ ያደርሳል!
ፈጣሪ ኢትየጵያንና ህዝቧን ይባርክ!


ከዚህ በታች *በዓባይ የኔ ነው* መጽሔት የቀረቡ አስተማሪና አስደማሚ ጽሁፎች መካከል ለናሙና ያህል በፎቶና በድምጽ አቅርበንላችኋል።

ከመስፍን ጳውሎስ