ፈጣን ምላሽ ለተራበው፣ለተጠማውና ለታረዘው ወገኔ !


ፈጣን ምላሽ ለተራበው፣ለተጠማውና ለታረዘው ወገኔ !

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በአሸባሪው የህውሃት ቡድን እኔ ወደ የመንግስት ስልጣን ካልተመለስኩ ሀገር ትፍረስ በሚል ዕብሪት በቀሰቀሰው ጦርነት ሳቢያ ሰላማዊው የሀገራች ህዝብ በአሰቃቂ ሁኔታ ለመገደል ፣ንብረቱን ለመዘረፍ፣ለመቁሰልና ለመሰደድ መዳረጉን የሰሙ በሀገርና ከገሀገር ውጭ የሚኖሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንን በከፍተኛ ቁጭትና ሀዘን ውስጥ ወድቀዋል። ይህ ቁጭትና ሀዘን እንቅልፍ የነሳቸው በመላው ዓለም የተለያዩ አገሮች የሚኖሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በግልና በተደራጀ መልኩ የገንዘብ፣ የምግብና የአልባሳት ዕርዳታ ማድረግ ላይ ሲረባረቡ ይስተዋላል።
የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ በሙኒክም ለተመሳሳይ ስራ በአካባቢው ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የወገን ለወገን ይድረስ ጥሪውን ፈጣን ምላሽ ለተራበው፣ለተጠማውና ለታረዘው ወገኔ በሚል መርህ

Oktober 31.2021
EineweltHouse
Schwanthale str. 80
80336 München
ከ12—18 ሰዓት

ጥሪውን ያቀረበ ስለሆነ በቦታው በመገኘት የዜግነት ግዴታችሁን ለመወጣት ዕድሉን እንድትጠቀሙበት ያስታውቃል።
*ማሳሰቢያ ወደ ዝግጅቱ ቦታ ሲመጡ በሀገሩ የCovid‐19 ወረርሺኝን አስመልክቶ በወጣው ህግ መሰረት በአጭሩ 3G-Regel መጠበቁን የሚያሳይ መረጃ ሊኖርዎት እንደሚገባና የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ በመያዝ እንዲመጡ ለማስታወስ እንወዳለን።
ሀገራችንና ህዝባችንን ፈጣሪ ይባርክ!