ለውድ የኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ በሙኒክ አባላት በሙሉ !

በቅድሚያ አክብሮታዊ ስላምታችንን እናቀርባለን!

ኮሚዩኒቲያችንን ለማጠናከር በሚደረገዉ እንቅስቃሴ ውስጥ ማኀበሩ የራሱ ድህረ ገጽ (Website) እንዲኖረው ታስቦ ሶሰት አባላት ያሉበት አንድ ኮሚቴ ከኮሚዩኒቲው የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ በትጋት በመንቀሳቅሰ ላይ ይገኛል።

ይህ አንቅስቃሴም ውጤታማ ሆኖ እነሆ ኮሚዩኒቲያችን የራሱ የሆነ ድህረ ገፅ (Website) መክፈቱን የምናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው!  ወደዚህ ውጤት ልንደርስ የቻልነው ከኢትዮ ሚዪኒክ ( http://www.ethiomunchen.de ) ድህረ ገጽ አዘጋጅ በተደረገልን ትብብር በመሆኑ የኮሚኒቲያችን አባልና የኢትዮሙኒክ ድህረ ገጽ ባለቤትን አቶ ወርቅነህ ክፍሌን ላደረጉልንና ወደፊትም ለሚያደርጉት እገዛና ተሳትፎ ይህን የሥራ ኃላፊነት ተቀብሎ በሚንቀሳቀሰው ኮሚቴና በእናንተ በኮሚዩኒቲው አባላት ስም ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን።

በድህረ ገፁ ላይ ምን ተግባራዊ ሆኗል?   ምንስ ሊስተናገድ ይችላል? 

  • የማሀበሩ ታሪክ፣ መረጃዎችና የተቀነባበሩ ዝግጅቶች ይሰነዱበታል፣ ይዘገቡበታል።
  • የአባልነት ክፍያና ሌሎች ክፍያዎችን ለማድረግ የኮሚዩኒቲው የባንክ አካውንት በቀላሉ ይገኛል።
  • አባል መሆን የሚፈልጉ በሙኒክ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተዘጋጀውን የአባልነት ቅጽ ኦንላይን (online) በመሙላት ከአመራር አካሉ ጋር በቀላሉ ግንኙነት ለመጀመር ይችላሉ።
  • አባላትና ቤተሰቦቻቸው ስለሀገራችን ስለኢትዮጵያ ታሪካዊና ወቅታዊ ሁኔታዎች እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎችን በማግኘት እንዲያነቡ፣ እንዲጽፉና መሰል ተሳትፎ እንዲያደርጉ የማስቻል እቅድ ይዞ በመነሳት ተግባራዊ ተደርጓል!
  • ኮሚዩኒቲያችንን ከመሰል ማኀበራትም ሆነ ከሌላው ዓለም ጋር ለማገናኘት ድልድይ ይሆናል።

በመሰረቱ ይህ ድህረ ገፅ ሊያድግና ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚችለው በተወስኑ ሰዎች ጥረት ብቻ ሳይሆን በዋናነት በአባላቱ ተሳትፎ ነውና ተሳትፏችሁን እንድታጎለብቱ እየጋበዝን ከዚህ በታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ድህረ ገፁን (Website) መጎብኘትና የተለያዩ ሕብረተሰባችንን ሊያስተምሩ፣ ሊያነቁና ሊያዝናኑ የሚችሉ ሰነጽሁፍ፣ ግጥምና ምስሎች፣ ተንቀሳቃሽ ምስሎች፣ የመሳስሉትን ከዚህ በታች ከድህረ ገጹ ጋር በተቀመጠው የኢሜል አደራሻ በመላክ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን። 

ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ፈጣሪ ይባርክ!

እናመሰግናለን

ድህረ ገፃችን: http://ethiomunichcommunity.de/           

E-Mail:       info@ethiomunichcommunity.de

ማሳሰቢያ

ማሳሰቢያ
በዚህ ድህረ ገፅ (Website) ላይ የሚወጣ ማናቸውም አስተያየት፣ ጽሁፍ፣ ግጥምና ምስል የማንኛውንም የህብረተስብ ክፍልም ሆነ ግለሰብ ስብዓዊ ክብርና መብት የሚጠብቅ፣ እኩልነትን የሚቀበል በጋራ መንፈስ ላይ ተመርኩዞ የሃገርን አንድነትና ሉአላዊነት የሚድግፍ ሃሳብ ብቻ መሆን እንዳለበት ከወዲሁ ግልጽ ማድረግ እንወዳለን።