ከመፃህፍት አለም ታላቁ ጥቁር ከተሰኘ መፅሐፍ የተወሰደ

ውድ በሙኒክ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ አባሎች

 ያለፈውን ከአቶ ንጉሴ ተካ „ታላቁ ጥቁር  “ መፅሃፍ የተወሰደ „ቅንጭብ“ ጽሁፍ ሳቀርብላችሁ ጽሁፌ የተቋጨው

„ለመሆኑ ቆንሲል ጄ. ስኪነር ወደ አቢሲኒያ ፣ወደ ምኒሊክ ሲሄድ ምን ይዞ ሄደ?

*ስኪነር ከስድስት ወር የአቢሲኒያ  ቆይታ በሁዋላ ለዘመናዊቷ ዩናይትድስቴትስ (ለፕሬዚዳንት ሩዝቬልት) ከምኒሊክ የተላከ ምን ስጦታ ይዞ ሄደ? „

በሚል ጥያቄ እንደሆነ ታስታውሳላችሁ ።

በዚሁ መሰረት በዚያ ሠዓት ማለትም  ከዛሬ 116 አመት በፊት ሁለቱ ሀገሮች የተለዋወጡት ስጦታ አቶ ንጉሴ እንደሚከተለው አቅርበውልናል።

„የአሜሪካው መልዕክተኛ ቡድን ለዳግማዊ ምኒልክ ያመጣውን ስጦታ አንድ ማለዳ ላይ ከቤተመንግሥት ተገኝቶ አበረከተ ። በእርግጥ በአሜሪካን መንግስት ታሪክ ለውጭ አገር መሪዎች ስጦታ ማበርከት የተለመደ ወግ አልነበረም ። ይህን ልማድ የያዙ በአብዛኛው በነገስታት ስርዓት የቆየ ባህል ያላቸው አገሮች በመሆናቸው እንዲያውም የአሜሪካን መንግሥት ልዑካን በፕሬዘዳንታቸው ስም ይህንን መሳይ ስጦታ ከዳግማዊ ምኒልክ ይዘው መቅረባቸው ያልተለመደ ነበር ማለት ይቻላል።አሜሪካኖቹ ከመምጣታቸው ጥቂት ቀደም ብሎ የእንግሊዝ ንጉሥ ለምኒልክ የሰለጠነ (ለማዳ) ዝሆን በሰጦታ ልከው ስለነበር ስመለከት አዲስ አበባ ውስጥ ተመልክቶ የተናገረውም ይሄንኑ ነበር።“ በማለት ስኪነር የተናገረውንምን አቶ ንጉሴ አስከትለው ገልጸውታል።

„የአሜሪካን ሪፑብሊክ ስጦታ የማበርከትም ሆነ የመቀበል ልማድ የለውም። ስለዚህም እኛ የእንግሊዙ ንጉሥ እንዳደረጉት ለየት ያለ ዝሆን አላመጣንም።ያመጠነው ለግርመዊነታቸው. አንዳንድ መታሰቢያ የሚሆኑ ነገሮችን ነው።እነርሱም አስደስቷቸዋል።…. „ብሏል።

ስኪነር በአገሩ ያመጣውን ስጦታ ለምኒልክ ሲያበረክት ያስቀደመው ፕሬዘዳንት ቴዲ ሩዝቬልት በእጃቸው „To Emeror Menelik, king of Abisinia,; Neguse Negest of Ethioia; from Theodore Roosevelt“ብለው የፈረሙበትን ፎቶግራፋቸውን ነበር።

ሩዝቬልት ለማስታወሻ መርጠው የላኩት ይህ ፎቶ ፕሮቶኮል የጠበቀ የሱፍ ኮት ለብሰው የተነሱትን ሰይሆን በስፓኒሽ‐አሜሪካን ጦርነት ላይ ከፍተኛ አዋጊ መኮንን ወይም የጦር መሪ ሆነው ከብዙ በፈፀሙበት መስክ የተነሱትን ፎቶ ነው።ይህም የእርሳቸውን ጀግንነ

ምኒሊክ እንደሰሙ ስለሚያውቁና በበኩላቸውም ምኒሊክ ባለ ድል የጥቁር አርበኞች መሪ በመሆናቸው ያስደስታቸዋል ከሚል መንፈስ የመነጨ ይመስላል ።

ስኪነር ይህን ፎቶ ለምኒሊክ ሲሰጣቸው በጣም ተደሰቱ ።ተቀብለውም የፕሬዘዳንቱን ምስል አለመኖሩና ሢያጤኑት ቆዩ። ከዚያም በአጠገባቸው ላሉት የጦር መኳንንቶች ፎቶውን ሰጧቸው።መኳንንቶቹም የፕሬዝዳንቱን መልክና ወታደራዊ አለባበስ በተመሳሳይ ስሜት ይመለከቱ ጀመር።

ስኪነር በማስከተል „North American big Game“በሚል ርእሰ ሩዝቬልት የፃፉትን መፅሐፍ ለምኒልክ አቀረበላቸው ።በአክብሮት ተቀበሉት። ፕሬዘዳንት ሩዝቬልት በወጣት እድሜያቸውብዙ ስራ መፈፀማቸውን ምኒሊክ በአድናቆት እንደተመለከቱት ስኪነር ጽፏል ። “ ሲሉ የ“ታላቁ ጥቁር“ መፅሀፍ ደራሲ አቶ ንጉሴ አየለ በማስረጃ ይገልፃሉ።

„ታላቁ ጥቁር „ገፅ 222

ውድ ወገኖቼ የአሜሪካን ለዳግማዊ ምኒሊክ የላኩዋቸውን ስጦታዎች ይህ ብቻ አይደለም።ሌሎቹን ስጦታዎችና በአፀፋው  ዳግማዊ ምኒሊክም ለአሜሪካን የላኩትን ስጦታዎች ስዕላዊ በሚመስል አጓጊ አገላለጽ የቀረበውን ክፍል ጊዜያችሁን ላለመሻማት በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ እንደማቀርብ በአክብሮት አየገለጽኩ አጋጣሚውን በመጠቀም እስከ አሁን ባካፈልኳችሁ አራት የመፅሀፉ „ቅንጭቦች“ ላይ በዚህ ግሩፕ ላይም ሆነ በግል አስተያየት የሰጣችሁኝን ሁሉ ከልብ ላመሰግን እወዳለሁ።

ቸር እንሰንብት።