124ኛው የአድዋ ድል በዓል በሙኒክ ጀርመን በድምቀት ተከብሮ ውሏል።

ፌብሪዋሪ 22 ቀን 2020 እ/ኤ/አ በጀርመን ከተማ በሙኒክ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአንድ ላይ ተሰባስበው 124ኛውን የአድዋ ድል በአል በሙኒክ የኢትዮጵያውያን ኮሚኒዩቲ አስተባባሪነት በደመቀ ሁኔታ አክብረዋል። በበአሉ ላይ በሙኒክና አካባቢው የሚኖሩ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከቤተሰቦቻቸው ጋር የተገኙ ሲሆን በተጨማሪ በጀርመን የኢፌዲሪ ኤምባሲን በመወከል በፍራንክፈርት የኢፌዲሪ ቆንስላ አምባሳደር በረደድ አንሙት በእንግድነት ተገኝተዋል። 

በአሉን በንግግር የከፈቱት በሙኒክ የኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ ሊ/መንበር ወ/ሮ ዘነብ ወርቅ አድነው ሲሆኑ በንግግራቸው የአድዋ ድል በዓል የኢትዮጵያውያን ድል ብቻ ሳይሆን የመላው ጥቁር ህዝቦች በአል ሆኖ አፍሪካውያን ሁሉ የሚኮሩበት ድል ሆኖ ሳለ በእኛው በኢትዮጵያውያን የተሰጠው ትኩረት የሚገባውን ያህል አለመሆኑ በተጻራሪው ታሪክን ለማኮሰስና በሎም ለማጥፋት ለሚሰሩ የውስጥም ሆነ የውጪ ጠላቶች አመቺ ሁኔታን ፈጥሯል በማለት ገልጸዋል። ከዚህም በተጭማሪ ተተኪው ትውልድ ታሪክን በአግባቡ እንዳይረዳና እንዳይረከብ ሆኗል። ስለዚህም አሁንም አለመርፈዱንና እኛ ወላጆች ጠንክረን ከሰራን ታሪካቸውን ለመረከብ የተዘጋጁ ለጆቻችን አሉና እኛ ከኛ የሚጠበቅብንን እንስራ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅረበዋል።

የማህበሩ ሊ/መንበር ለበዓሉ በእንግድነት የተጋበዙት በጀርመን የኢፌዲሪ አምባሳደር በስራ ፕሮግራም ምክንያት መገኘት ባይችሉም እሳቸውን በመወከል የተገኙትን በፍራንክፈርት የኢፌዲሪ ቆንስላ አምባሳደር በረደድ አንሙትን ለንግግር ጋብዘዋል።

አምባሳደሩ ሰለሃገር ማለት ምን ማለት እንደሆነና ኢትዮጵያውያን በተለይም በውጪ ሃገር የሚኖሩ   የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በመሰባሰብና በመደራጀት ብዙ መስራት እንደሚችሉ ታሪካቸውንም ለትውልድ በማስተላለፍና ለሌሎችም በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና መጫወት እንደሚችሉ አስረድተው አጋጣሚውን በመጠቀም መንገስት በአዲስ መልክ በየከታማዎች ከሚገኙ ኮሚዩኒቲዎችና መሰል ተቋሞች ጋር ተቀርቅርቦ ለመስራት ሁኔታዎችን ያመቻቸ መሆኑን ገልጸዋል።

በዓሉ በዋናነት ለአድዋ ጦርነት ምክንያት በሆነው በውጫሌ ውል ላይ የተመረኮዘ አጭር ትያትር የታየ ሲሆን በማስከተል የግጥምና የወጣቶች የተለያዩ ትዕይንቶች ቀርበዋል። በተጭማሪ በዚሁ በሙኒክ ከተማ ነዋሪ የሆኑ በሁለት ኢትዮጵያውያን እህቶች የኪነ ጥበብ ስራዎችን ያቀረቡ ሲሆን እነዚህም   በኮሚዩኒቲው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የገ/ያዥ ወ/ሮ ጌጤ አለማየሁ የተጣሉ የተለያዩ የወይን፣የለስላሳና አልክሆል መጠጦች መሽጫ ጠርሙሶችን በልዩ ሁኔታ በማስጌጥ ለቤትና ለቢሮዎች ዴኮሬሽንነት እንዲውሉ ያዘጋጁዋቸው ስራዎቻቸው ለህዝብ እይታና ልማህበሩ ገቢ እንዲሆን ለሺያጭ የቀረቡ ሲሆን ሌላዋ የስነጥበብ ሴት ወ/ሮ ሃይማኖት መሰለም ባላቸው የስዕል መሳል ችሎታ የሰሯቸውን በርካታ ስዕሎች ለህዝብ ዕይታና ሺያጭ አቅርበዋል።ክስዕሎቻቸው መካከልም አንዱና የተወዳጁን የአድዋ ድል መሪ የአጼ ምኒሊክን ምስል በቶምቦላ ሺያጭ የተገኘው ገንዘብ ለኮሚዩኒቲው ገቢ የሆን ዝንድ አበርክተዋል።ከዚህ በተረፈ በሙኒክ የኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ የስራ አስኪያጅ ኮሜቴ አስተባባሪነት የተዘጋጁ የምግብና የመጠጥ ዝግጅቶች በጥሩ ዋጋ ቀርቦ ታዳሚዎች ከነቤተስቦቻቸው በአሉን የደመቀና የሞቀ በአል ሆኖ እንዲያከብሩት አስችሏል።