በጀርመን አገር በሙኒክ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደኢትዮጵያዊያን በሀገራቸውየኮሮናቫይረስ ወረርሺኝን ለመከላከል እንዲቻል 8558,00€ የገንዝብ እርዳታ አደረጉ

በጀርመን አገር በሙኒክ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንደ ሌሎች በውጭ አገር የሚኖሩ ወገኖቻቸው በኢትዮጵያ የኮረና ቫይረስ ወረርሺኝን ለመከላከል በሚደረገው ርብርብ ላይ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ከፍራንክፈርት የኢፌዲሪ ኮንሱላት ጽ/ቤት የቀረበውን የዜግነት ጥሪ መነሻ በማድረግ በየኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ በሙኒክ አስተባባሪነት ባለፉት ሳምንታት በኦን ላይን (Online) የተጀመረው የገንዘብ እርዳታ ማሰባሰብ የደረሰበትን ደረጃ በሚመለከት የእያንዳንዱ ልገሳ ያደረጉ ወገኖችን ስምና የለገሱትን የገንዘብ መጠን የታዳጊ ወጣቶችን አስተዋፅኦ ጭምር በዝርዝር ለህብረተሰቡ ግልጽነት ባለው መንገድ በሰንጠርዥ በማቅረብ አሳውቀዋል ።
» Weiterlesen