ከሰው ማሣ አትጨድ!

ተዋናይ ፣ አዘጋጅ ፣ ገጣሚ እና አርቲስት ፣ የጣይቱ የባህል ማዕከል በዋሺንግተን ዲሲ መስራች አለም ፀሃይ ወዳጆ ከሰው ማሣ አትጨድ! ከሰው ማሳ አትጨድ …የንጥቂያ ከፍታ መሬት ታውላለች፤እያንዳንዷ ውጤት …እያንዳንዷ ፍሬ ዋጋ አስከፍላለች፡ጥረህ ግረህ ብላ …እንደ መፅሐፉ ቃል፡ዛሬም ባይሆን ነገ የሰው ወዙ ያንቃል፤አፈሩን ጎልጉሎ … ቆፍሮ አረስርሶ፡ዘርቶ ተንከባክቦ ….ከእንቅልፉ ቀንሶ፤ለዝናብ አንጋጦ ….ፀሐይን ተማልዶ፡መዳፉን አሻክሮ …ልምዱን አዋሕዶ፤በውኑም በእንቅልፉም ፡ሲያስብ ከርሞበታል፡ፍሬው እስኪያፈራ ፡ ሥቃይ ቆጥሮበታል፤ከሰው ማሳ አትጨድ ! …በጨለማ ተገን ፤ እንዳይቀጨው አውሬ፡እንዳያዳባየው ፡ ረግጦ ተራምዶበትግድ አይሰጠው ጥሬ …አጥሮ ጠብቆት ነው ውጤት ሆኖ አብቦ ይህ ያየኸው ዛሬ፤እያንዳንዷ ውጤት …እያንዳንዷ ፍሬ ዋጋ አስከፍላለች፡ከሰው ማሳ አትጨድ …የንጥቂያ ከፍታ መሬት ታውላለች፤ጥረህ ግረህ ብላ …እንደ መፅሃፉ ቃል፡ዛሬም ባይሆን ነገ …. የሰው ወዙ ያንቃል፤በግንባር ፡ በላብህ በጉልበትህ ጥረት ፡በራስህ ተመንደግ በድካምህ ውጤትከሰው ማሣ አትጨድ…ዝም ብሎ አላፈራም እንዲያው እንደዘበት … ዘለህ አትፈሰው…ንቀህ ወይ ዘንግተህ የደከመበትን የፈጠረውን … ሰው ፤በየቱም ሙያ መስክ …በምንም ሥራ ላይደክመህ መመንደግ ነው … ከልብ የሚያረካው .. ስትውል ከበላይጤና ተገብሮ ተስፋ ተሰንቆ ፡በቁር በሐሩሩ …. ተጥሎ ተወድቆ፤የጋሬጣ ፍቀት … ያደማ እሾህ ታልፎ ፡የለማ ፍሬ ነው …ከዕድሜ ላይ ተቀርፎ ፤ከሰው ማሣ አትጨድ !

» Weiterlesen

ለውድ የኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ በሙኒክ አባላት በሙሉ !

በቅድሚያ አክብሮታዊ ስላምታችንን እናቀርባለን! ኮሚዩኒቲያችንን ለማጠናከር በሚደረገዉ እንቅስቃሴ ውስጥ ማኀበሩ የራሱ ድህረ ገጽ (Website) እንዲኖረው ታስቦ ሶሰት አባላት ያሉበት አንድ ኮሚቴ ከኮሚዩኒቲው የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ በትጋት በመንቀሳቅሰ ላይ ይገኛል። ይህ አንቅስቃሴም ውጤታማ ሆኖ እነሆ ኮሚዩኒቲያችን የራሱ የሆነ ድህረ ገፅ (Website) መክፈቱን የምናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው!  ወደዚህ ውጤት ልንደርስ የቻልነው ከኢትዮ ሚዪኒክ ( http://www.ethiomunchen.de ) ድህረ ገጽ አዘጋጅ በተደረገልን ትብብር በመሆኑ የኮሚኒቲያችን አባልና የኢትዮሙኒክ ድህረ ገጽ ባለቤትን አቶ ወርቅነህ ክፍሌን ላደረጉልንና ወደፊትም ለሚያደርጉት እገዛና ተሳትፎ ይህን የሥራ ኃላፊነት ተቀብሎ በሚንቀሳቀሰው ኮሚቴና በእናንተ በኮሚዩኒቲው አባላት ስም ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን። በድህረ ገፁ ላይ ምን ተግባራዊ ሆኗል?   ምንስ ሊስተናገድ ይችላል?  የማሀበሩ ታሪክ፣ መረጃዎችና የተቀነባበሩ ዝግጅቶች ይሰነዱበታል፣ ይዘገቡበታል። የአባልነት ክፍያና ሌሎች ክፍያዎችን ለማድረግ የኮሚዩኒቲው የባንክ አካውንት በቀላሉ ይገኛል። አባል መሆን የሚፈልጉ በሙኒክ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተዘጋጀውን የአባልነት ቅጽ ኦንላይን (online) በመሙላት ከአመራር አካሉ ጋር በቀላሉ ግንኙነት ለመጀመር ይችላሉ። አባላትና ቤተሰቦቻቸው ስለሀገራችን ስለኢትዮጵያ ታሪካዊና ወቅታዊ ሁኔታዎች እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎችን በማግኘት እንዲያነቡ፣ እንዲጽፉና መሰል ተሳትፎ እንዲያደርጉ የማስቻል እቅድ ይዞ በመነሳት ተግባራዊ ተደርጓል! ኮሚዩኒቲያችንን ከመሰል ማኀበራትም ሆነ ከሌላው ዓለም ጋር ለማገናኘት ድልድይ ይሆናል። በመሰረቱ ይህ ድህረ ገፅ ሊያድግና ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚችለው በተወስኑ ሰዎች ጥረት ብቻ ሳይሆን በዋናነት በአባላቱ ተሳትፎ ነውና ተሳትፏችሁን እንድታጎለብቱ እየጋበዝን ከዚህ በታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ድህረ ገፁን (Website) መጎብኘትና የተለያዩ ሕብረተሰባችንን ሊያስተምሩ፣ ሊያነቁና ሊያዝናኑ የሚችሉ ሰነጽሁፍ፣ ግጥምና ምስሎች፣ ተንቀሳቃሽ ምስሎች፣ የመሳስሉትን ከዚህ በታች ከድህረ ገጹ ጋር በተቀመጠው የኢሜል አደራሻ በመላክ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን።  ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ፈጣሪ ይባርክ! እናመሰግናለን ድህረ ገፃችን: http://ethiomunichcommunity.de/            E-Mail:       info@ethiomunichcommunity.de ማሳሰቢያ ማሳሰቢያበዚህ ድህረ ገፅ (Website) ላይ የሚወጣ ማናቸውም አስተያየት፣ ጽሁፍ፣ ግጥምና ምስል የማንኛውንም የህብረተስብ ክፍልም ሆነ ግለሰብ ስብዓዊ ክብርና መብት የሚጠብቅ፣ እኩልነትን የሚቀበል በጋራ መንፈስ ላይ ተመርኩዞ የሃገርን አንድነትና ሉአላዊነት የሚድግፍ ሃሳብ ብቻ መሆን እንዳለበት ከወዲሁ ግልጽ ማድረግ እንወዳለን።

» Weiterlesen