ከእኛ ወዲያ ለእኛ

በሙኒክ የኢትዮጵያውያን ኮሙዩኒቲ ማህበር በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተከፈተው ህግን የማስከበር ዘመቻ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ነዋሪዎችና የመከላከያ ሰራዊት የማቴሪያልና የገንዘብ ድጋፍ የማድረጉ ስራ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ በሚኖሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ርብርብ መደረጉንና እየተደረገ መሆኑን ይታወቃል ። በዚሁ መሰረት በሙኒክና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙኒክ የኢትዮጵያውያን ኮሙዩኒቲ „ከእኛ ወዲያ ለእኛ “ በሚል መርህ ባደረገላቸው የድጋፍ ጥሪ መሰረት 4000.00 € ይህም ወደ የኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር በግምት ወደ 192,000 ሺህ የኢትዮጵያ ብር መሰብሰቡንና ይህም ገንዘብ ለዚሁ ጉዳይ በኢትዮጵያ ወደ ተከፈተው የባንክ ሂሳብ በቀጥታ ገቢ የተደረገ መሆኑን የኮሚዩኒቲው የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ በኮሚዩኒቲው የማህበራዊ መገናኛ መድረክ ላይ የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉትን ወገኖችን ስምና የክፍያ መጠን ከያዘ ዝርዝር መረጃ ጋር ግልጽነት በሚንጸባረቅበት መልኩ በማቅረብ አሳውቋል። ሀገራችን ኢትዮጵያን ከጥፋት ወገኖቻችን ከመከራ ይሰውርልን!ሀገራችን ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኑር!

» Weiterlesen