ግድቡ የኔ ነው!

በመስፍን ጳውሎስ የህዳሴ ግድቡ ስራ መጠናቀቅ የአንድ ብሄር፣ሀይማኖት ወይም የፖለቲካ አመለካከት ያለው ህብረተሰብ ብቻ ፍላጎት ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያውያን መሆኑ ግልጽ ነው።ከዚህ የግድብ ስራ ጋር የተያያዙ እንቅስቃሴዎች ላይ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተግባራዊ አስተዋጽኦ ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው በያሉበት ከሚያደርጉት እንቅስቃሴዎች መገንዘብ ይቻላል።በዚሁ መሰረት በጀርመን አገር የህዳሴውን ግድብ ስራ ድጋፍ በሚመለከት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ማስተባበር የሚያስችል የተለያዩ ህብረተሰባችንን ከሚወክሉ ልዩ ልዩ ማህበራትና ታዋቂ ወገኖች የተካተቱበት ግብረሃይል ተቋቁሞ ስራ የጀመረ ሲሆን ግብረሃይሉ ከነደፋቸው ዘርፈ ብዙ የስራ ዕቅዶቹ አንዱ የህዳሴውን ግድብ አስመልክቶ በተለያዩ የታሪክ፣የጥናትና ሌሎች የስነፅሁፍ ውጤቶችን በመፅሔት መልክ በማሳተም ህብረተሰባችን ስለዓባይ ወንዝና ስለህዳሴ ግድብ ያለውን ግንዛቤ እንዲያሳድግና ከመፅሄቱም ሺያጭ የሚገኘውን ትርፍ ለህዳሴው ግድብ ስራ ማዋል እንዲያስችል ማድረግ በመሆኑ የተለያዩ በጀርመን የሚኖሩ ሀገር ወዳድ ወገኖችን በማስተባበር? * ግድቡ የኔ ነው * የሚል ርዕስ የተሰጠው መፅሔት ለህትመት እንዲበቃ ተደርጎ በየአካባቢው በሚገኙ የተለያዩ የኢትዮጵያውያን ማህበራት ተሰራጭቶ በመሸጥ ላይ ይገኛል።ስለዚህም ሀገሩን የሚወድ ዜጋ ሁሉ ትንሿን አስተዋፅኦ እንዲያደርግ አመቺ ሁኔታን የፈጠረ መሆኑን በመግለጽ የሙኒክና አካባቢው የኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ መጽሔቱን በደመቀ መርሀ ግብር አዘጋጅቶ ለማስተዋወቅና ለመሸጥ ዝግጅት እያደረገ መሆኑና እስከዚያው መጽሔቱን ለማከፋፈል ከወከላቸው የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላት መግዛት እንደሚቻል በማህበራዊ ሜዲያ ገልጿል።ስለዚህም ሀገር ወዳድ የሆንን ወገኖች ሁሉ ይህን „ግድቡ የኔ ነው“ የሚሰኝ መፅሐፀት ለራሳችንና ለሌሎች ወዳጆቻችን ገዝተን በስጦታነት በማበርከት አሻራችንን ለማሳረፍ እንድንችል ተጋብዘናልና ከግብዣው እንቋደስ። የኢትዮጵያ ህዝብ የህዳሴን ግድብ በመተባበርና በቁርጠኝነት ለፍፃሜ ያደርሳል!ፈጣሪ ኢትየጵያንና ህዝቧን ይባርክ! ከዚህ በታች *በዓባይ የኔ ነው* መጽሔት የቀረቡ አስተማሪና አስደማሚ ጽሁፎች መካከል ለናሙና ያህል በፎቶና በድምጽ አቅርበንላችኋል።

» Weiterlesen

የወንድማችን የአቶ ብሩክ ማሞ የመታሰቢያ ሃውልት ምርቃት

በሙኒክ ነዋሪ የነበረው ሀገር ወዳዱ ወንድማችን አቶ ብሩክ ማሞ ወደ ውድ ሀገሩ ወደ ኢትዮጵያ ሄዶ ባደረበት ድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም መለየቱን አስመልክቶ ኮሚዩኒቲያችን አስተባባሪነት በኖቬምበር 14 ቀን 2020 እኤአ የፀሎትና የስንብት ስነስርዓት መደረጉ ይታወሳል ። በዚህ ስነስርዓት ላይ ከወዳጅ ጓደኞቹ ጥያቄ በመነሳት  ለወንድማችን የአቶ ብሩክ ማሞ የመታሰቢያ ሀውልት ማሰሪያ ይሆን ዘንድ በኮሚዩኒቲያችን በኩል የተሰበሰበውን (2000.00Euro) 100.000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ለቤተሰቦቹ አስተላልፈን አነሆ የሀውልቱ ስራ ተጠናቆ ቤተሰቦቹ በተገኙበት የተመረቀ መሆኑን የምናሳውቃችሁ ላሳያችሁት ወገናዊ ትብብር ከልብ በማመስገን  ነው። የወንድማችንን ነፍስ ይማር!  ለቤተሰቦቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን ይስጥልን!  በሙኒክ የኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ

» Weiterlesen

ከእኛ ወዲያ ለእኛ

በሙኒክ የኢትዮጵያውያን ኮሙዩኒቲ ማህበር በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተከፈተው ህግን የማስከበር ዘመቻ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ነዋሪዎችና የመከላከያ ሰራዊት የማቴሪያልና የገንዘብ ድጋፍ የማድረጉ ስራ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ በሚኖሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ርብርብ መደረጉንና እየተደረገ መሆኑን ይታወቃል ። በዚሁ መሰረት በሙኒክና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙኒክ የኢትዮጵያውያን ኮሙዩኒቲ „ከእኛ ወዲያ ለእኛ “ በሚል መርህ ባደረገላቸው የድጋፍ ጥሪ መሰረት 4000.00 € ይህም ወደ የኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር በግምት ወደ 192,000 ሺህ የኢትዮጵያ ብር መሰብሰቡንና ይህም ገንዘብ ለዚሁ ጉዳይ በኢትዮጵያ ወደ ተከፈተው የባንክ ሂሳብ በቀጥታ ገቢ የተደረገ መሆኑን የኮሚዩኒቲው የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ በኮሚዩኒቲው የማህበራዊ መገናኛ መድረክ ላይ የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉትን ወገኖችን ስምና የክፍያ መጠን ከያዘ ዝርዝር መረጃ ጋር ግልጽነት በሚንጸባረቅበት መልኩ በማቅረብ አሳውቋል። ሀገራችን ኢትዮጵያን ከጥፋት ወገኖቻችን ከመከራ ይሰውርልን!ሀገራችን ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኑር!

» Weiterlesen

የአቶ ብሩክ ማሞ አጭር የሕይወት ታሪክ

2 Timothy 4:7-8 / 2ኛ ጢሞ 4 ፣ 7-8Ich habe den guten Kampf gekämpft, den Lauf vollendet, den Glauben bewahrt; hinfort liegt für mich die Krone der Gerechtigkeit bereit; መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ I have fought the good fight, I have finished the race, I have kept the faith. Henceforth there is laid up for me the crown of righteousness, which the Lord, the righteous judge, will award to me on that day በወ/ሮ እናኑ ጌታሁን የቀረበ ወንድማችን አቶ ብሩክ ማሞ ወይም በክርስትና ስሙ ተክለ አረጋዊ ሰኔ 6 ቀን 1955 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለደ። በአዲስ አበባ ቢወለድም የወጣትነት እድሜዉንና ትምህርቱን የተከታትለው በቀደሞ ስሙ በጅባትና ሜጫ አውራጃ በአምቦ ክተማ ነዉ። እንደማንኛውም ህጻን በዚያን ዘመን በቄስ ት/ቤ ፊደል ቆጥሮ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በአምቦ ት/ቤት በጥሩ ሁኔታ ስላጠናቀቀ፣ የ2ተኛ ደረጃ ትምህርቱን በአዲሰ አበባ ጄኔራል ዊንጌት አዳሪ ት/ቤት ለመማር እድል አገኝቶ ለ4 ዓመታት ትምህርቱን ተከታትሏል። በጥሩ ውጤትም አጠናቋል።  

» Weiterlesen

ከሰው ማሣ አትጨድ!

ተዋናይ ፣ አዘጋጅ ፣ ገጣሚ እና አርቲስት ፣ የጣይቱ የባህል ማዕከል በዋሺንግተን ዲሲ መስራች አለም ፀሃይ ወዳጆ ከሰው ማሣ አትጨድ! ከሰው ማሳ አትጨድ …የንጥቂያ ከፍታ መሬት ታውላለች፤እያንዳንዷ ውጤት …እያንዳንዷ ፍሬ ዋጋ አስከፍላለች፡ጥረህ ግረህ ብላ …እንደ መፅሐፉ ቃል፡ዛሬም ባይሆን ነገ የሰው ወዙ ያንቃል፤አፈሩን ጎልጉሎ … ቆፍሮ አረስርሶ፡ዘርቶ ተንከባክቦ ….ከእንቅልፉ ቀንሶ፤ለዝናብ አንጋጦ ….ፀሐይን ተማልዶ፡መዳፉን አሻክሮ …ልምዱን አዋሕዶ፤በውኑም በእንቅልፉም ፡ሲያስብ ከርሞበታል፡ፍሬው እስኪያፈራ ፡ ሥቃይ ቆጥሮበታል፤ከሰው ማሳ አትጨድ ! …በጨለማ ተገን ፤ እንዳይቀጨው አውሬ፡እንዳያዳባየው ፡ ረግጦ ተራምዶበትግድ አይሰጠው ጥሬ …አጥሮ ጠብቆት ነው ውጤት ሆኖ አብቦ ይህ ያየኸው ዛሬ፤እያንዳንዷ ውጤት …እያንዳንዷ ፍሬ ዋጋ አስከፍላለች፡ከሰው ማሳ አትጨድ …የንጥቂያ ከፍታ መሬት ታውላለች፤ጥረህ ግረህ ብላ …እንደ መፅሃፉ ቃል፡ዛሬም ባይሆን ነገ …. የሰው ወዙ ያንቃል፤በግንባር ፡ በላብህ በጉልበትህ ጥረት ፡በራስህ ተመንደግ በድካምህ ውጤትከሰው ማሣ አትጨድ…ዝም ብሎ አላፈራም እንዲያው እንደዘበት … ዘለህ አትፈሰው…ንቀህ ወይ ዘንግተህ የደከመበትን የፈጠረውን … ሰው ፤በየቱም ሙያ መስክ …በምንም ሥራ ላይደክመህ መመንደግ ነው … ከልብ የሚያረካው .. ስትውል ከበላይጤና ተገብሮ ተስፋ ተሰንቆ ፡በቁር በሐሩሩ …. ተጥሎ ተወድቆ፤የጋሬጣ ፍቀት … ያደማ እሾህ ታልፎ ፡የለማ ፍሬ ነው …ከዕድሜ ላይ ተቀርፎ ፤ከሰው ማሣ አትጨድ !

» Weiterlesen