በጀርመን አገር በሙኒክ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ፈጣን ምላሽ ለወገኔ በሚል ዝግጅት ከ15,000.00 € (አስራ አምስት ሺህ ዩሮ)በላይ አሰባሰቡ።

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በአሸባሪው የህውሃት ቡድን እኔ ወደ የመንግስት ስልጣን ካልተመለስኩ ሀገር ትፍረስ በሚል ዕብሪት በቀሰቀሰው ጦርነት ሳቢያ ሰላማዊው የሀገራች ህዝብ በአሰቃቂ ሁኔታ ለመገደል ፣ንብረቱን ለመዘረፍ፣ለመቁሰልና ለመሰደድ መዳረጉን የሰሙ በሀገር ውስጥና ከገር ውጪ የሚኖሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ቁጭትና ሀዘን ውስጥ ወድቀዋል።እነዚህ ይህ ቁጭትና ሀዘን እንቅልፍ የነሳቸው በመላው ዓለም የተለያዩ አገሮች የሚኖሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በግልና በተለያዩ  መልክ ተደራጅተው የገንዘብ፣ የምግብና የአልባሳት ዕርዳታ ማሰባሰብና ለተጎጂዎች በማድረስ ላይ ሲረባረቡ ይስተዋላል። የኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ በሙኒክና አካባቢው ስር የተደራጁ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም እንደ ሌሎች ሀገር ወዳድ ወገኖቻቸው በወቅቱ የሀገራችን ጉዳይ ላይ መክረው በተደራጀ  የኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲያቸው አስተባባሪነት የበኩላቸውን ለማድረግ በመነሳሳት ሁለት የዕርዳታ ማሰባቢያ ዕቅዶችን በማስቀመጥ ተንቀሳቅሰዋል። 1ኛው..ሀገርን የማዳን አስቸኳይ ጥሪ  በሚል መርህ ላይ የተመሰረተ ሲሆን።በየወሩ ለአንድ ዓመት የሚዘልቅ ለሀገርና ለወገን ለመድረስ የሚያስችል  የገንዘብ እርዳታ የማሰባሰብ እንቅስቃሴ ሲሆን2ኛው.ፈጣን ምላሽ ለተራበው፣ለተጠማውና ለታረዘው ወገኔ !* በሚል መርህ  ላይ የተመሰረተና ሀገር ወዳዶች የሚያደርጉትን በአንድ ጊዜና በአፋጣኝ የሚለግሱትን የገንዘብ ዕርዳታ ማሰባሰብ ነው።በእነዚህ  በሁለቱም ዕቅዶች መሰረት የተደረገው እንቅስቃሴ እጅግ አመርቂ የሆነ ውጤት መገኘቱን ከዝግጅቱ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ሲገልጹ*ፈጣን ምላሽ ለተራበው፣ለተጠማውና ለታረዘው ወገኔ*በሚለው መርህ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ በሙኒክ በአካባቢው ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የወገን ለወገን ይድረስ ጥሪውንበኦክቶበር 31.2021 ባዘጋጀው ልዩ ዝግጅት ከ15,000.00€ (አስራ አምስት ሺህ ዩሮ) በላይ ለማሰባሰብ መቻሉንና በሌላ በኩል በ1ኛ ደረጃ በተቀመጠው ዕቅድ መሰረት ሀገራችን የምትገኝበትንን እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ኮሚዪኒቲው ሀገር ወዳድ ወገኖችን በማስተባበር በየወሩ እንደ መነሻ  50€ (ሃምሳ ዩሮ) አየተዋጣ  ለአንድ አመት የሚዘልቅ የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ከጀመረ እነሆ ሶስተኛ ወሩን መያዙንና የሚያበረታታ ውጤት እየታየበት መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።በዚህ ለአንድ አመት የገንዘብ መዋጮ ላይ መሳተፍ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከዚህ መልዕክት ጋር በተቀመጠው ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የባንክ አካውንት በየወሩ የተቻላቸውን ያህል Dauerauftrag ፣ ወይም የአመት፣ ሩብ አመት፣የስድስት ወር በማስተላለፍ  መሳተፍ የሚችሉ መሆኑም በተጨማሪ ተገልጿል።  ይህ በሙኒክና አካባቢው ኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ ከጥቂት ወራት በፊት *ደግሞ ለአባይ* በሚል ልዪ የግሪል ዝግጅት አዘጋጅቶ የቦንድ ሽያጭና የገንዘብ ልገሳ፣እንዲሁም የምግብና የመጠጥ ሺያጭ በጥቅሉ ከ20,000.00€(ሃያ ሺህ ዩሮ)  በላይ አሰባስቦ ለሚመለከተው ክፍል ማስተላለፉም ተገልጿል። ከሀገራችንና ከህዝባችን ጎን ለመቆምና እንደ ዜጋ የበኩላችንን ለመወጣት ከህሊናችን በስተቀር የማንንም ፈቃድ ወይም ይሁንታ አያስፈልገንም!!የህዝባችንን ህይወት ለመታደግ የምናቀርበው ምንም ምክንያት የለንም!!!ለዚህም የሰላም አባት የሆነው!ፈጣሪያችን ይረዳናል! ሀገራችንና ህዝባችንን ፈጣሪ ይባርክ! ማሳሰቢያ ከላይ በተገለጹት ሁለት መንገዶች ለሀገርና ለወገን የሚደረግ እርዳታ የአቅማችሁን በማድረግ ሰብአዊና ወገናዊ ሃላፊነታችሁን ለመወጣት የምትፈልጉ ሁሉ ለጉዳዩ የተዘጋጁትን የባንክ መረጃዎችን ከዚህ በታች ያስቀመጥንላችሁ መሆኑን በትህትና እንገልፃለን።

» Weiterlesen

ታሪክ ሰርቶ ማለፍ

በመስፍን ጳውሎስ  ውድ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን በምንኖርበት በጀርመን አገር በሙኒክ ከተማ ኗሪ የነበሩትና የሀገራችን የኢትዮጵያን ታሪክ ለኢትዮጵያውያንና ለሌሎች በአለም ዙሪያ ያሉ ሕዝቦች የማስተዋወቅ ስራ ለብዙ አመታት ሲሰሩ የነበሩት አቶ ግርማ ፍስሃ ዕድሜያቸው ደርሶ ጡረታ ሲወጡ ቀሪ ዘመናቸውን በሚወዷት ሀገራቸው እንዲሆን በመወሰን ከውድ ቤተሰቦቻቸውና ዘመዶቻቸው ጋር ሲኖሩ ቆይተው በህመም ምክንያት ከዚህ አለም በሞት እስከተለዩበት ድረስ ለሀገራቸው ባላቸው አቅምና ችሎታ የሚቻላቸውን ሁሉ ሲያደርጉ በመቆየታቸው ታሪክ ሲዘክራቸው ይኖራል ። አቶ ግርማ ፍስሐ ስላደረጉት የሀገርን ማስተዋወቅ ስራ በአንድ ወቅት ከታዋቂው የሸገር ሬዲዮ „ስንክሳር“ የሚሰኝ ዝግጅት ላይ „የሙኒኩ ተንቀሳቃሽ ቤተመዘክር“ በሚል ርዕስ የቀረበውን ዝግጅት ምናልባትም ከጥቂቶች በቀር  ብዙዎቻችን የማናውቀውን የወንድማችንን የአቶ ግርማ ፍስሀን ከፊል የህይወት ጉዞ፣ዝርዝር ሥራዎችና የሀገራችን ታሪክ እንድናውቅ ይረዳል ብለው ያመኑ ሀገር ወዳድ ወገኖች ከሰጡን አስተያየት በመነሳት እኛም በሀሳቡ ስላመንበት የወንድማችንን ህልፈት የ40ቀን መታሰቢያ በማድረግ በኮሚዩኒቲያችን ስም ልናካፍላችሁ ወደናልና ከዚህ ጽሁፍ በታች የተቀመጠውን የድምጽ ማጫወቻ  በመክፈት እንድትከታተሉት በማክበር ጋብዘናችኋል። በዚህ አጋጣሚም አቶ ግርማ ፍስሀን በጀርመን አገር በሙኒክ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንደ ነዋሪ ብዙዎች እንደሚያውቋቸው ግልፅ ነው። ነገር ግን ይህን ያህል ጠለቅ ብሎ ያደረጉትን እንቅስቃሴና ጥረት  ለሀገራቸው ያበረከቱትን አስተዋፅኦ የሚያውቁ ምን ያህሉ ናቸው? በእውነትስ ብዙዎች „አብረን እንኖር ነበር እንጂ ለካ አናውቃቸውም ነበር! “ ሳያሰኛቸው ይቀራል? “ ብለን የአቶ ግርማ ፍስሀን ታሪክ መነሻ በማድረግ ሰፋ አድርግን አይተን የሚቀጥለውን ጥያቄ ለአንባቢያን እናቀርባለን በዓለም ዙሪያ በሚኖሩ የኢትዮጵያውያን ኮሙዩኒቲዎች መሀከል የሚገኙ እንደ አቶ ግርማ ፍስሃ ያሉ ብዙ ቁምነገርን የሰሩ ልምድና ዕውቀቱ ያላቸው ወገኖችን አብሮ ከመኖር በዘለቀ ምን ያህል ጠለቅ ብለን እናውቃቸዋለን? ማንም ሰው ቀኑ ሲደርስ ያልፋልና ከማለፋቸው በፊትስ ታሪካቸውን፣ያደረጉትን ጥረትና የሰሩትን ስራ፣የፈፀሙትን ገድል እንዲያካፍሉን ዕድሉን እያመቻቸንላቸውስ ነው? ስንቶችስ ብዙ ነገር ሰርተው ታሪካቸው ሳይታወቅ ትውልድ ሳይማርበት እንደ ዘበት አልፈዋል?  የሚለውን ጥያቄ ይህ ጽሁፍ ለሚያነቡ ሁሉ በማቅረብ ውድ ኢትዮጵያውያን በያሉበት በግልም ሆነ በተደራጀ መልክ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ሊወያዩበትና ሊንቀሳቀሱበት ይገባል እንላለን። በመጨረሻም ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት የአቶ የግርማ ፍስሃን የረጂም ዘመን ለሀገር የተደረገ ጥረት ወንድማችን በህይወት እያሉ ቃለመጠይቅ በማድረግ አቶ ግርማ ፍስሀ ከዚህ ዓለም በሞት ቢለዩም ታሪካቸው ለትውልድ ለማስተላለፍ ያስቻሉትን የሸገር ራዲዮ „ስንክሳር „ዝግጅት አዘጋጅ ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይንና ባልደረባውን ወንጌላዊት ብርሃኑን እንደተቋምም የሸገር ሬዲዮ ጣቢያን በሙኒክ የኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ ስም ልናመሰግን እንወዳለን።የወንድማችንን ነፍስ ይማር!ለቤተሰቦቻቸው ፣ዘመድ ወዳጆቻቸው መፅናናትንና ጥንካሬን ይስጥልን!መልካም የማድመጥ ጊዜ እንመኛለን ።

» Weiterlesen

ለውድ የኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ በሙኒክ አባላት በሙሉ !

በቅድሚያ አክብሮታዊ ስላምታችንን እናቀርባለን! ኮሚዩኒቲያችንን ለማጠናከር በሚደረገዉ እንቅስቃሴ ውስጥ ማኀበሩ የራሱ ድህረ ገጽ (Website) እንዲኖረው ታስቦ ሶሰት አባላት ያሉበት አንድ ኮሚቴ ከኮሚዩኒቲው የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ በትጋት በመንቀሳቅሰ ላይ ይገኛል። ይህ አንቅስቃሴም ውጤታማ ሆኖ እነሆ ኮሚዩኒቲያችን የራሱ የሆነ ድህረ ገፅ (Website) መክፈቱን የምናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው!  ወደዚህ ውጤት ልንደርስ የቻልነው ከኢትዮ ሚዪኒክ ( http://www.ethiomunchen.de ) ድህረ ገጽ አዘጋጅ በተደረገልን ትብብር በመሆኑ የኮሚኒቲያችን አባልና የኢትዮሙኒክ ድህረ ገጽ ባለቤትን አቶ ወርቅነህ ክፍሌን ላደረጉልንና ወደፊትም ለሚያደርጉት እገዛና ተሳትፎ ይህን የሥራ ኃላፊነት ተቀብሎ በሚንቀሳቀሰው ኮሚቴና በእናንተ በኮሚዩኒቲው አባላት ስም ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን። በድህረ ገፁ ላይ ምን ተግባራዊ ሆኗል?   ምንስ ሊስተናገድ ይችላል?  የማሀበሩ ታሪክ፣ መረጃዎችና የተቀነባበሩ ዝግጅቶች ይሰነዱበታል፣ ይዘገቡበታል። የአባልነት ክፍያና ሌሎች ክፍያዎችን ለማድረግ የኮሚዩኒቲው የባንክ አካውንት በቀላሉ ይገኛል። አባል መሆን የሚፈልጉ በሙኒክ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተዘጋጀውን የአባልነት ቅጽ ኦንላይን (online) በመሙላት ከአመራር አካሉ ጋር በቀላሉ ግንኙነት ለመጀመር ይችላሉ። አባላትና ቤተሰቦቻቸው ስለሀገራችን ስለኢትዮጵያ ታሪካዊና ወቅታዊ ሁኔታዎች እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎችን በማግኘት እንዲያነቡ፣ እንዲጽፉና መሰል ተሳትፎ እንዲያደርጉ የማስቻል እቅድ ይዞ በመነሳት ተግባራዊ ተደርጓል! ኮሚዩኒቲያችንን ከመሰል ማኀበራትም ሆነ ከሌላው ዓለም ጋር ለማገናኘት ድልድይ ይሆናል። በመሰረቱ ይህ ድህረ ገፅ ሊያድግና ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚችለው በተወስኑ ሰዎች ጥረት ብቻ ሳይሆን በዋናነት በአባላቱ ተሳትፎ ነውና ተሳትፏችሁን እንድታጎለብቱ እየጋበዝን ከዚህ በታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ድህረ ገፁን (Website) መጎብኘትና የተለያዩ ሕብረተሰባችንን ሊያስተምሩ፣ ሊያነቁና ሊያዝናኑ የሚችሉ ሰነጽሁፍ፣ ግጥምና ምስሎች፣ ተንቀሳቃሽ ምስሎች፣ የመሳስሉትን ከዚህ በታች ከድህረ ገጹ ጋር በተቀመጠው የኢሜል አደራሻ በመላክ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን።  ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ፈጣሪ ይባርክ! እናመሰግናለን ድህረ ገፃችን: http://ethiomunichcommunity.de/            E-Mail:       info@ethiomunichcommunity.de ማሳሰቢያ ማሳሰቢያበዚህ ድህረ ገፅ (Website) ላይ የሚወጣ ማናቸውም አስተያየት፣ ጽሁፍ፣ ግጥምና ምስል የማንኛውንም የህብረተስብ ክፍልም ሆነ ግለሰብ ስብዓዊ ክብርና መብት የሚጠብቅ፣ እኩልነትን የሚቀበል በጋራ መንፈስ ላይ ተመርኩዞ የሃገርን አንድነትና ሉአላዊነት የሚድግፍ ሃሳብ ብቻ መሆን እንዳለበት ከወዲሁ ግልጽ ማድረግ እንወዳለን።

» Weiterlesen

በጀርመን አገር በሙኒክ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደኢትዮጵያዊያን በሀገራቸውየኮሮናቫይረስ ወረርሺኝን ለመከላከል እንዲቻል 8558,00€ የገንዝብ እርዳታ አደረጉ

በጀርመን አገር በሙኒክ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንደ ሌሎች በውጭ አገር የሚኖሩ ወገኖቻቸው በኢትዮጵያ የኮረና ቫይረስ ወረርሺኝን ለመከላከል በሚደረገው ርብርብ ላይ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ከፍራንክፈርት የኢፌዲሪ ኮንሱላት ጽ/ቤት የቀረበውን የዜግነት ጥሪ መነሻ በማድረግ በየኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ በሙኒክ አስተባባሪነት ባለፉት ሳምንታት በኦን ላይን (Online) የተጀመረው የገንዘብ እርዳታ ማሰባሰብ የደረሰበትን ደረጃ በሚመለከት  የእያንዳንዱ ልገሳ ያደረጉ ወገኖችን ስምና የለገሱትን የገንዘብ መጠን የታዳጊ ወጣቶችን አስተዋፅኦ ጭምር በዝርዝር ለህብረተሰቡ ግልጽነት ባለው መንገድ በሰንጠርዥ በማቅረብ አሳውቀዋል ።

» Weiterlesen

ከመፃህፍት አለም ታላቁ ጥቁር ከተሰኘ መፅሐፍ የተወሰደ

ከዚህ ቀጥሎ በተለያዩ ክፍሎች የሚቀርቡት ጽሁፎች ከዚህ በላይ በምስል ከተቀመጠው ከለመድናቸውና ካነበብናቸው ለየት ያሉ ያልተሰሙ የአድዋ ድልና የአጤ ምኒሊክ ታሪኮችን ይዞ ለህዝብ ከቀረበው የአቶ ንጉሴ አየለ ተካ ‚ታላቁ ጥቁር ‚ የተሰኘ መፅሐፍ የተወሰዱ መሆናቸውን አስቀድመን ለመግለፅ እንወዳለን ። ልክ በዛሬው ቀን ፌብሩዋሪ 1,1094 እኤአ የምዕራቡ ዓለም ሪፓርተሮች ምን ዘገቡ? ሮበርት ስኪነርና አብረውት የነበሩት ባልደረቦቹ ከኢትዮጵያ ድሬዳዋ ፣ በጂቡቲ ከዚያም በቪክቶሪያ በተሰኘች መረከብ  አድርገው. ስኪነር ከ5አመታት በላይ ወደ ሰራባት ማርሴይ (ፈረንሳይ) ሲደርስ በፓሪስ የአሜሪካን ኤምባሲ ተወካይና  ብዙ ሌሎች ሠዎች „እንኳን ደህና መጣህ“ ለማለት ተሰብስበዋል ።ከስድስት ወራት በላይ የተለያት ባለቤቱ ሄለንም ነበረች።ነገር ግን ስለኢትዮጵያና ስለ ጥቁሩ የአቢሲኒያ ንጉስ ለመስማትና ሪፖርት ለማድረግ የተሰበሰቡት  የአውሮፓና የአሜሪካን የዜና ሪፓርተሮች ቦታውን አጨናንቀውት ነበር። ስኪነር በሪፓርተሮች ተከበበ!

» Weiterlesen

124ኛው የአድዋ ድል በዓል በሙኒክ ጀርመን በድምቀት ተከብሮ ውሏል።

ፌብሪዋሪ 22 ቀን 2020 እ/ኤ/አ በጀርመን ከተማ በሙኒክ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአንድ ላይ ተሰባስበው 124ኛውን የአድዋ ድል በአል በሙኒክ የኢትዮጵያውያን ኮሚኒዩቲ አስተባባሪነት በደመቀ ሁኔታ አክብረዋል። በበአሉ ላይ በሙኒክና አካባቢው የሚኖሩ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከቤተሰቦቻቸው ጋር የተገኙ ሲሆን በተጨማሪ በጀርመን የኢፌዲሪ ኤምባሲን በመወከል በፍራንክፈርት የኢፌዲሪ ቆንስላ አምባሳደር በረደድ አንሙት በእንግድነት ተገኝተዋል።  በአሉን በንግግር የከፈቱት በሙኒክ የኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ ሊ/መንበር ወ/ሮ ዘነብ ወርቅ አድነው ሲሆኑ በንግግራቸው የአድዋ ድል በዓል የኢትዮጵያውያን ድል ብቻ ሳይሆን የመላው ጥቁር ህዝቦች በአል ሆኖ አፍሪካውያን ሁሉ የሚኮሩበት ድል ሆኖ ሳለ በእኛው በኢትዮጵያውያን የተሰጠው ትኩረት የሚገባውን ያህል አለመሆኑ በተጻራሪው ታሪክን ለማኮሰስና በሎም ለማጥፋት ለሚሰሩ የውስጥም ሆነ የውጪ ጠላቶች አመቺ ሁኔታን ፈጥሯል በማለት ገልጸዋል። ከዚህም በተጭማሪ ተተኪው ትውልድ ታሪክን በአግባቡ እንዳይረዳና እንዳይረከብ ሆኗል። ስለዚህም አሁንም አለመርፈዱንና እኛ ወላጆች ጠንክረን ከሰራን ታሪካቸውን ለመረከብ የተዘጋጁ ለጆቻችን አሉና እኛ ከኛ የሚጠበቅብንን እንስራ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅረበዋል።

» Weiterlesen

የኢትዮጵያ አዲስ አመት 2012 ዓ/ም በሙኒክ ከተማ በድምቀት ተከብሯል

ethiopian new year 2012

በጀርመን አገር በሙኒክ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በጥቅምት 1 ቀን 2012 ዓ/ም ( እኤአ በኦክቶበር 12.2019) በኮሚኒዩቲያቸው አስተባባሪነት በኢትዮጵያውያን የዘመን አቆጣጠር አዲሱን ዓመት 2012ዓ/ምን  ባንድ ላይ ተስባስበው ቤተስባዊ መልክ ባለውና በደመቀ ሁኔታ አክብረዋል።

» Weiterlesen